قۆرئان بتنێ

1

يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡمُدَّثِّرُ

አንተ (ልብስ) ደራቢው ሆይ!



3

وَرَبَّكَ فَكَبِّرۡ

ጌታህንም አክብር::


4

وَثِيَابَكَ فَطَهِّرۡ

ልብስህንም አጥራ::


5

وَٱلرُّجۡزَ فَٱهۡجُرۡ

ጣዖትንም ራቅ::


6

وَلَا تَمۡنُن تَسۡتَكۡثِرُ

ማብዛትንም የምትፈልግ ሆነህ አትለግስ::



8

فَإِذَا نُقِرَ فِي ٱلنَّاقُورِ

በቀንዱም በተነፋ ጊዜ፤


9

فَذَٰلِكَ يَوۡمَئِذٖ يَوۡمٌ عَسِيرٌ

ይህን ጊዜ ያ ቀን አስቸጋሪ ቀን ነው።


10

عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ غَيۡرُ يَسِيرٖ

(በተለይ) በከሓዲያን ላይ ገር ያልሆነ ቀን ነው።



12

وَجَعَلۡتُ لَهُۥ مَالٗا مَّمۡدُودٗا

ለእርሱም የተዘረጋን ገንዘብ (በዓይነቱ) አደረግኩለት።



14

وَمَهَّدتُّ لَهُۥ تَمۡهِيدٗا

ለእርሱም ኑሮውን መዘርጋትን ዘረጋሁለት፤


15

ثُمَّ يَطۡمَعُ أَنۡ أَزِيدَ

ከዚያ ልጨምርለት ይከጅላል::


16

كَلَّآۖ إِنَّهُۥ كَانَ لِأٓيَٰتِنَا عَنِيدٗا

ሰው ይከልከል! እርሱ ለአናቅጻችን በእርግጥ ተቃዋሚ ነበርና።



18

إِنَّهُۥ فَكَّرَ وَقَدَّرَ

እርሱ (በቁርኣን ጉዳይ) አሰበ፤ ገመተም።


19

فَقُتِلَ كَيۡفَ قَدَّرَ

እናም ተረገመ:: እንዴት ገመተ!


20

ثُمَّ قُتِلَ كَيۡفَ قَدَّرَ

ከዚያ ተረገመ። እንዴትስ ገመተ!



22

ثُمَّ عَبَسَ وَبَسَرَ

ከዚያ ፊቱን አጨፈገገ አኮማተረም::


23

ثُمَّ أَدۡبَرَ وَٱسۡتَكۡبَرَ

ከዚያ (በአላህ ከማመን) ዞረ:: ኮራም::


24

فَقَالَ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا سِحۡرٞ يُؤۡثَرُ

«ይህ ከሌላ (ሰው) የሚቀዳ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም።


25

إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا قَوۡلُ ٱلۡبَشَرِ

«ይህ የሰው ቃል እንጂ ሌላ አይደለም» አለ::




28

لَا تُبۡقِي وَلَا تَذَرُ

(ያገኘችውን ሁሉ) አታስቀርም:: አትተዉምም::


29

لَوَّاحَةٞ لِّلۡبَشَرِ

የሰዎችን ቆዳ በጣም አክሳይ ናት።


30

عَلَيۡهَا تِسۡعَةَ عَشَرَ

በእርሷም ላይ አስራ ዘጠኝ (ዘበኞች) አሉባት::


31

وَمَا جَعَلۡنَآ أَصۡحَٰبَ ٱلنَّارِ إِلَّا مَلَٰٓئِكَةٗۖ وَمَا جَعَلۡنَا عِدَّتَهُمۡ إِلَّا فِتۡنَةٗ لِّلَّذِينَ كَفَرُواْ لِيَسۡتَيۡقِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ وَيَزۡدَادَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِيمَٰنٗا وَلَا يَرۡتَابَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡمُؤۡمِنُونَ وَلِيَقُولَ ٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٞ وَٱلۡكَٰفِرُونَ مَاذَآ أَرَادَ ٱللَّهُ بِهَٰذَا مَثَلٗاۚ كَذَٰلِكَ يُضِلُّ ٱللَّهُ مَن يَشَآءُ وَيَهۡدِي مَن يَشَآءُۚ وَمَا يَعۡلَمُ جُنُودَ رَبِّكَ إِلَّا هُوَۚ وَمَا هِيَ إِلَّا ذِكۡرَىٰ لِلۡبَشَرِ

የእሳትን ዘበኞች መላዕክት እንጂ ሌላ አላደረግንም:: ቁጥራቸውንም ለእነዚያ በአላህ ለካዱት ሰዎች መፈተኛ እንጂ ለሌላ አላደረግንም:: እነዚያ መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች እንዲያረጋግጡ፤ እነዚያም በትክክል ያመኑት እምነትን እንዲጨምሩ፤ እነዚያም መጽሐፍን የተሰጡትና ምዕመናኖቹ እንዳይጠራጠሩ፤ እነዚያም በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው አስመሳዮችና ከሓዲያን «አላህ በዚህ (ቁጥር) ምን ምሳሌ ሽቷል?» እንዲሉ እንጂ (አላደረግንም):: ልክ እንደዚሁ አላህ የሚፈልገውን ያጠማል:: የሚፈልገውንም ያቀናል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህንም ሰራዊት ልክ ከእርሱ በስተቀር ማንም አያውቅም:: የሰቀር እሳት ለሰዎች መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም::



33

وَٱلَّيۡلِ إِذۡ أَدۡبَرَ

በሌሊቱም በሄደ ጊዜ፤


34

وَٱلصُّبۡحِ إِذَآ أَسۡفَرَ

በንጋቱም ባበራ ጊዜ እምላለሁ።


35

إِنَّهَا لَإِحۡدَى ٱلۡكُبَرِ

(ሰቀር) ከታላላቆች አደጋዎች አንዱ፤


36

نَذِيرٗا لِّلۡبَشَرِ

ለሰዎች አስፈራሪ ናት።


37

لِمَن شَآءَ مِنكُمۡ أَن يَتَقَدَّمَ أَوۡ يَتَأَخَّرَ

ከናንተ መካከል ወደ በጎ ነገር መቅደምን ወይም ወደ ኋላ መቅረትን ለፈለገ (ሰው) ሁሉ፤


38

كُلُّ نَفۡسِۭ بِمَا كَسَبَتۡ رَهِينَةٌ

ነፍስ ሁሉ በሰራችው ስራ ተያዥ ናት::




41

عَنِ ٱلۡمُجۡرِمِينَ

ከአመጸኞች ሁኔታ (ይጠያየቃሉ)



43

قَالُواْ لَمۡ نَكُ مِنَ ٱلۡمُصَلِّينَ

«ከሰጋጆች አልነበርንም።


44

وَلَمۡ نَكُ نُطۡعِمُ ٱلۡمِسۡكِينَ

«ለድሆችም የምናበላም አልነበርንም።


45

وَكُنَّا نَخُوضُ مَعَ ٱلۡخَآئِضِينَ

«ከዘባራቂዎችም ጋር እንዘባርቅ ነበር።


46

وَكُنَّا نُكَذِّبُ بِيَوۡمِ ٱلدِّينِ

«በፍርዱ ቀንም እናስተባብል ነበር፤


47

حَتَّىٰٓ أَتَىٰنَا ٱلۡيَقِينُ

«እርግጠኛው ነገር ሞት እስከመጣብን ድረስ።» ይላሉ


48

فَمَا تَنفَعُهُمۡ شَفَٰعَةُ ٱلشَّٰفِعِينَ

እናም በዚያ ቀን የአማላጆች (ሁሉ) ምልጃ አትጠቅማቸዉም።


49

فَمَا لَهُمۡ عَنِ ٱلتَّذۡكِرَةِ مُعۡرِضِينَ

ከ(ቁርኣን) ከግሳጼም የሚያፈገፍጉበት ምን ምክኒያት አላቸው?


50

كَأَنَّهُمۡ حُمُرٞ مُّسۡتَنفِرَةٞ

እነርሱ ልክ ደንባሪዎች የሜዳ አህዩች ይመስላሉ::


51

فَرَّتۡ مِن قَسۡوَرَةِۭ

ከአንበሳ የሸሹ


52

بَلۡ يُرِيدُ كُلُّ ٱمۡرِيٕٖ مِّنۡهُمۡ أَن يُؤۡتَىٰ صُحُفٗا مُّنَشَّرَةٗ

ይልቁንም ከእነርሱ መካከል ለእያንዳንዱ ሰው የተዘረጉ ጹሑፎችን በእጁ እንዲሰጥ ይፈልጋል::



54

كَلَّآ إِنَّهُۥ تَذۡكِرَةٞ

ይከልከሉ፤እርሱ(ቁርአን) መገሰጫ ነው።



56

وَمَا يَذۡكُرُونَ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُۚ هُوَ أَهۡلُ ٱلتَّقۡوَىٰ وَأَهۡلُ ٱلۡمَغۡفِرَةِ

ሆኖም (ሰዎች) አላህ ካልፈለገ በስተቀር አይገሰጹም:: አላህ የመፈራት ባለቤት ነው:: (ለፈሩትም) የምህረት ባለቤት ነው::


تەفسیر هاتە کۆپی کرن